የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል ምረቃን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የሚዲያ ካፕ ውድድር እየተከናወነ ይገኛል።

0
287

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢቢሲ ጊቢ በሚገኘው የእግር ኳስ ሜዳ እየተካሄደ ባለው ውድድር በዛሬው መርሐ ግብር አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተጫውተዋል።

ውድድሩን በምክትል ሥራ አሥፈጻሚ ማዕረግ የኮርፖሬሽኑ የቋንቋዎች ዘርፍ ኃላፊ ሙክታር ሁሴን፣ የአሚኮ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ እና የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ሰጠኝ አቦሃይ አስጀምረውታል።

በሚድያ ካፕ ውድድሩ ኢቢሲ፣ አሚኮ፣ ፋና፣ አዲስ ዋልታ፣ ፕራይም ሚዲያ፣ አዲስ ሚዲያ፣ ኤንቢሲ እና ኦቢኤ ተሳታፊ መኾናቸውን የኢቢሲ መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here