ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ፡፡ ጎል ዶት ኮም በምድብ ጨዋታዎች በተካሄዱ 36 ጨዋታዎች ለሀገራቸው ምርጥ ብቃት ያሳዩ 11 ተጨዋቾችን አሳውቋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
በግብ ጠባቂ፡- ጂያንሉጂ ዶናሩማ (ከጣሊያን)
በተከላካዮች፡- ዳኒ ካርቫሃል (ከስፔን)፣ ማርክ ጉይ (ከእንግሊዝ)፣ ሪካርዶ ካላፊዮሪ (ከጣሊያን)፣ ማክሲሚሊያን ሚቴሊስታድ (ከጀርመን) በአማካይ፡- ፋቢያን ሩይዝ (ከስፔን)፣ ማርሴል ሳቢቲዘር (ከኦስትሪያ)፣ ጀማል ሙሲያላ (ከጀርመን)
በአጥቂ፡- ላሚን ያማል (ከስፔን)፣ ጆርጌስ ሚካውታድዝ (ከጆርጂያ)፣ ኒኮ ዊሊያምስ (ከስፔን) በየቦታቸው ምርጥ ተብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!