እንጅባራ: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአቀባበል ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባንጃ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ እና የስፖርት ምክር ቤት ሠብሣቢ ሞላ ወሌ ክለቡ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ ለውጤት በመብቃቱ ምሥጋና አቅርበዋል። ክለቡ ቀጣይ በሚኖረው ተሳትፎ ወረዳ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡
የክለቡ አሠልጣኝ ሰውበሰው ታደሰ ክለቡ በውድድር ዘመኑ በስፖርተኞች ብርቱ ጥረት እና በስፖርት ቤተሰቦች ድጋፍ ለስኬት መብቃቱን ተናግረዋል። በእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች እና በወረዳው የሥራ ኀላፊዎች የተደረገላቸው አቀባበል ለተሻለ ሥራ የሚያነሳሳቸው መኾኑንም አሠልጣኙ ገልጸዋል።
ክለቡ ለውጤት እንዲበቃ ድጋፍ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማትም አሠልጣኙ ምሥጋና አቅርበዋል።ክለቡ በወረዳው ስፖርት ምክር ቤት እና በግል ባለሃብቶች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶለታል። ክለቡ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፕሪምየር ሊግ አማራ ክልልን በመወከል ተሳታፊ እንደሚኾንም ታውቋል።
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!