ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር አንድ ቀን ቀርቶታል። ዋንጫውን ማን ያነሳል የሚለው ብዙዎችን እያነጋገረም ነው። በቅርቡ የፌነርባቼ አሠልጣኝ የኾኑት ጆዜ ሞሪንሆም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
አነጋጋሪው ሰው ፖርቱጋል ዋንጫውን ታነሳለች ብለዋል። ይህን ያሉትም ፖርቱጋል ሀገራቸው ስለኾነች አድልተው ሳይኾን ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች በሁሉም ቦታ ስለያዘች ነው በሚል።
ጆዜ እንግሊዝን የዋንጫ ተፋላሚ እንደምትኾንም ገምተዋል። ሀሪ ኬን የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ፣ ጁዲ ቤሊንግሀም ደግሞ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ይኾናል ብለው ገምተዋል ሲል ዩሮ ስፓርት አስነብቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!