ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጣሊያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ የሴሪኤው ክለብ ናፖሊ አሠልጣኝ ኾነው ተቀጥረዋል፡፡ እስከ 2027 የሚያቆያቸውን የሦስት ዓመት ውልም ተፈራርመዋል፡፡

0
239

የናፖሊ ቡድን ፕሬዝዳንት ኦሬሊዮ ዴ ላውረንቲስ “አንቶኒዮ ኮንቴ ብርቱ አሠልጣኝ ነው” ብለዋል። የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን ያሠለጠኑት ኮንቴ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በመጋቢት 2023 ቶተንሃምን ከለቀቁ በኋላ ከሥራ ርቀው ቆይተዋል፡፡

በ2017 የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ከቼልሲ ጋር ያነሱት ኮንቴ ለናፖሊ ይፋዊ ድረ ገጽ ”ለቡድኑ ዕድገት ከድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ጋር የተቻለኝን ሁሉ በማድረግ የናፖሊን ከፍታ ለመጨመር ቃል እገባለሁ” ብለዋል፡፡ ናፖሊ በ2023/24 የሴሪኤው የውድድር ዘመን 10ኛ ኾኖ በማጠናቀቁ ኮንቴ ከፍተኛ ሥራ ይጠብቃቸዋል ነው የተባለው፡፡

ስካይ ስፖርት በድረ ገጹ እንዳስነበበው ኮንቴ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2005 ጀምሮ 11 ቡድኖችን አሠልጥነዋል፡፡ ከስመ ጥሩዎቹ መካከል ከጣሊያን አታላንታን፣ ጁቬንቱስ፣ ኢንተር ሚላን ያሠለጠኑ ሲኾን በእንግሊዝ ደግሞ ቼልሲ እና ቶትንሃምን አንቶኒዮ ኮንቴ ማሠልጠናቸው ይታወሳል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here