ምባፔ የአምስት ዓመት ውል ዛሬ ፈረመ።

0
203

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ25 ዓመቱ ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ የሀገሩን ቡድን ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ለቅቆ የስፔኑን ሪያል ማድሪድ መቀላቀሉን በፊርማው አረጋግጧል። በሪያል ማድሪድ የሚያቆየውን የአምስት ዓመት ውል ዛሬ ሰኞ አመሻሽ ላይ ፈርሟል።

ኪሊያን ምባፔ ፊርማው ካስቀመጠ በኋላ “ሕልሜ እውን ኾኗል” ብሏል። ተጫዋቹ በፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የነበረው ኮንትራት በሰኔ 30/2024 በመጠናቀቁ ወደ በርናባው ስታዲየም አምርቷል ተብሏል። ምባፔ “አሁን ምን ያህል እንደተደሰትኩ ማንም ሊረዳኝ አይችልም!” ሲል በኢንስታግራም ገጹ ላይ ማስፈሩን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here