የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ሥብሥብ ይፋ ኾነ።

0
312

ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች ተለይተዋል።

በዚህ መሰረት በግብ ጠባቂነት ፍሬው ጌታሁን፣ ሰይድ ሐብታሙ እና አቡበከር ኑራ፣ በተከላካይ ቦታ ረመዳን የሱፍ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ብርሀኑ በቀለ፣ ፍቅሩ አለማየሁ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ፍሬዘር ካሳ፣ ጊት ጋትኩት እና ያሬድ ካሳየ ተመርጠዋል።

ፉአድ ፈረጃ ፣ ቢንያም አይተን፣ አብዱልከሪም ወርቁ፣ ቢንያም በላይ፣ ብሩክ ማርቆስ፣ አብነት ደምሴ፣ ጋቶች ፓኖም እና ወገኔ ገዛኸኝ ደግሞ የመሀል ተጫዋቾች ናቸው። አጥቂዎች ከነዓን ማርክነህ፣ መስፍን ታፈሰ፣ ቢንያም ፍቅሩ እና ምንይሉ ወንድሙ ኾነዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ ጊኒ ቢሳው የሚያመራ ይኾናል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here