ፌነርባቼ ጆሴ ሞሪንሆን አሠልጣኝ አድርጎ ቀጠረ።

0
258

ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ጆሴ ሞሪንሆ የቱርኩን የእግር ኳስ ቡድን ፌነርባቼን ለማሠልጠን በሁለት ዓመት ውል ተስማምተዋል። ፌነርባቼ በቱርክ ሱፐር ሊግ ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመታት ሁለተኛ ኾኖ ያጠናቀቀ ቡድን ስለኾነ በ2024/2025 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ለማድረግ ሞሪንሆ ብርቱ ሥራ ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

ሞሪንሆ ከአሠልጣኝነታቸው ጎን ለጎን እግር ኳስን አሳብበው በሚሰጧቸው አወዛጋቢ አስተያዬቶች እና ትችቶች ይታወቃሉ፤ ይፈራሉም። ሰውዬው እግር ኳስ ማሠልጠን ከጀመሩ 24 ዓመት የኾናቸው ሲኾን ፌነርባቼ ደግሞ 11ኛ የሚያሠለጥኑት ቡድን ኾኖ ተመዝግቧል ሲል ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

ሞሪንሆ ከጣሊያኑ ሮማ ቡድን በጥር ወር ከተባረሩ በኋላ ሥራ ፈተው መቆየታቸው ይታዎሳል። አወዛጋቢው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ ቼልሲን፣ ሪያል ማድሪድን፣ ኢንተርሚላንን፣ ቶተንሃምን እና ማንቸስተር ዩናይትድን እና ሮማን ማሠልጠናቸው አይዘነጋም።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here