ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ የሚያደርጉት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ጨዋታው የሚካሄድበት ስታዲየም በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ ቡና ሀዋሳ ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ መድንን በግማሽ ፍጻሜው በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፋቸው ይታወቃል። የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!