አትሌት ሱቱሜ አሰፋ የኦሎምፒክ ቡድንን እንድትቀላቀል ተወሰነ።

0
286

ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰሞኑን በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈውን ቡድን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይሁን እና አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በቡድኑ ባለመካተቷ ቅሬታ አቅርባ ነበር። በዚህም መሠረት የአትሌቷ ቅሬታ ተቀባይነት በማግኘቱ ዛሬ አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ወደሚገኙበት ሆቴል እንድትቀላቀል ተወስኗል።

ሱቱሜ አሰፋ በ2024ቱ የቶኪዮ ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏ ይታወሳል። በተጨማሪም በሕንድ ኮልካታ ከተማ በተደረገው ግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here