ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካኝ ካሲሚሮ በበርካታ የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ቡድኖች እየተፈለገ ነው፡፡ የ32 ዓመቱን ብራዚላዊ አማካይ ካሲሚሮ በክረምቱ የዝውውር ወቅት ማንቸስተር ዩናይትድን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል። ማንቸስተር ዩናይትድም ተጫዋቹን ለመሸጥ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው እየተነገረ ነው፡፡ ታዲያ የሳዑዲ አረቢያ ቡድኖች ማለትም አል ናስር፣ አል አህሊ እና አል ቃሲዲያን ዋነኛ የተጫዋቹ ፈላጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡
ስካይ ስፖርት “ብራዚላዊው ካሲሚሮ ከመካከለኛው ምሥራቅ ቡድኖች አንዱን ለመቀላቀል ከፍተኛ ጉጉት አድሮበታል” ሲል አስነብቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!