ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አሠልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን የማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ምትክ አድርጎ ለመሾም እየተነጋገረ ነው፡፡ አሠልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ወደ ቼልሲ ቡድን የመሄድ ፍላጎታቸውን ለሌስተር ሲቲ የበላይ ኀላፊዎች አሳውቀው መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡ ይሁን እና ሌስተር ሲቲ የውል ማፍረሻ 10 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
የቼልሲ ቡድን የስፖርት ተባባሪ ዳይሬክተር ፖል ዊንስታንሌይ እንዳሉት ቼልሲ የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ነው። የ44 ዓመቱ ጣሊያናዊው ኤንዞ ማሬስካ ከዓመት በፊት ሌስተርን ተረክበው ወደ ፕሪምየር ሊጉ መልሰውታል።አሁን ቼልሲ በአምስት ዓመት ውል ሊያስፈርማቸው ጫፍ መድረሱን ስካይ ስፖርት አስነብበቧል።ማሬስካ በማንቸስተር ሲቲ በአካዳሚ ደረጃ እንዲሁም በፓርማ የአሠልጣኝነት ልምድ አላቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!