ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳዳር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ሰይድ አራጋው የሠራተኞች የስፖርት ውድድር ዋና ዓላማው በሠራተኞች መካከል ወንድማማችነትን ማምጣት ነው ብለዋል፡፡ ሠራተኞች በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በመሳተፍ ጤናቸውን በመጠበቅ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እንድኾኑ ማስቻል ነው ብለዋል።
ውድድሩን እያካሄድን ያለነው በከተማችን ሰላም ስላለ ነው፡፡ ይሄንኑ የስፖርት ቤተሰብ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፋለሁ ብለዋል። በውድድሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአቢሲኒያ ባንክ ለፍጻሜ የተገናኙ ሲሆን መደበኛውን የጨዋታ ጊዜ አንድ እኩል አጠናቅቀው በመጨረሳቸው ንግድ ባንክ በመለያ በማሸነፍ የዋንጫ እና የብር ተሸላሚ ኾኗል። ከእግር ኳስ በተጨማሪ የገመድ ጉተታ ውድድር መካሄዱን የደሴ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!