አሠልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ውላቸውን አራዘሙ፡፡

0
208

ባሕር ዳር: ግንቦት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ስፔናዊው አሠልጣኝ ኡናይ ኢምሬ በአስቶን ቪላ እስከ 2029 የሚቆዩበትን ውል አራዝመዋል፡፡ በ2023/24 የውድድር ዘመን አስቶንቪላን በአስደናቂ አቋም ለቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እንዲበቃ ያደረጉት ኡናይ ኢምሬ የክለቡ ኀላፊዎች እንዲቆዩላቸው ፈልገዋል፡፡ በሊጉ ታላላቅ ክለቦች ያላሳኩትን የቻምፕዮንስ ሊግ ቦታን ያገኙት አሠልጣኙ አድናቆት እየተቸራቸው ነው፡፡

የ52 ዓመቱ ስፔናዊ አሠልጣኝ በ2022 ከቪያሪያል ወደ አስቶን ቪላ ሲመጡ ክለቡ በወራጅ ቀጣና ስጋት ውስጥ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ከእርሳቸው መምጣት በኋላ ግን አስቶን ቪላ በብዙ መልኩ ተቀይሯል፡፡ በመጡበት ዓመት ከወራጅ ቀጣና ስጋት አውጥተው ሰባተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ያደረጉት አሠልጣኙ በሁለተኛው ዓመት ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ አድርገውታል፡፡ በክለቡ ኀላፊነት በመውሰዳቸው እና ክለቡን በማሠልጠናቸው ደስተኛ መኾናቸውንም አሠልጣኙ ገልጸዋል፡፡

የአስቶን ቪላው ሊቀመንበር ናሲፍ ሳዋሪስ በአስቶን ቪላ ልዩ ነገር እየገነባን ነው፤ ኡናይን እስከ 2029 ድረስ በክለቡ ለማቆዬት በመፈራረማችን ተደስተናል ብለዋል፡፡ ከኡናይ የሚጠብቁት ብዙ ነገር እንዳለም ተናግረዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here