አንቶኒዮ ኮንቴ የናፖሊ አሠልጣኝ ለመኾን ተቃርበዋል።

0
287

ባሕር ዳር: ግንቦት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

የጣሊያኑ ናፖሊ ባለፈው የውድድር ዓመት የጣሊያን ሴሪኤ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዓመት ደካማ የውድድር ጊዜን አሳልፏል።

ይህን ተከትሎ የክለቡን ተፎካካሪነት ለመመለስ አዲስ አሠልጣኝ ለመቅጠር አስቧል። በጁቬንቱስ እና ቼልሲ ቤት ዋንጫ ማሳካት የቻሉት አንቶኒዮ ኮንቲ ደግሞ የክለቡ ምርጫ ኾነዋል። አሁን ላይ ያለ ሥራ የሚገኙት ጣሊያናዊ አሠልጣኝም ቀጣዩ የናፖሊ አሠልጣኝ ለመኾን መስማማታቸው የዋን ፉትቦል መረጃ ያሳያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here