ባርሴሎና ዣቪን አሰናበተ።

0
205

ባሕር ዳር: ግንቦት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባርሴሎና አሠልጣኝ ዣቪ ሄርናንዴዝን አሰናብቷል፡፡ ስፔናዊው የቀድሞ የባየርን ሙኒክ እና የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ እርሳቸውን ለመተካት በሂደት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ የስፔን ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ተጫዋች የነበረው ዣቪ በጥር ወር ኑካፕን እንደሚለቁ ቢያሳውቁም በሚያዝያ ወር የቡድኑ ፕሬዚዳንት ጆአን ላፖርታ እስከ 2025 ድረስ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸው ይታዎሳል፡፡

በመኾኑም የ44 ዓመቱ ዣቪ ለመጪው የውድድር ዘመን እቅድ በማውጣት ላይ ነበሩ ነው የተባለው፡፡ ለዣቪ ስንብት ምክንያቱ ከሰሞኑ ስለቡድኑ የፋይናንስ አወጣጥ ጉዳይ ሐሳብ መስጠታቸው እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ ይህን ተከትሎም ከቡድኑ ፕሬዚዳንት ጆአን ላፖርታ እና ከስፖርት ዳይሬክተሩ ዲኮ ጋር እሰጥ አገባ በገጠሙ ማግስት ነው የተሰናበቱት ፡፡

ዣቪ በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታውን የፊታችን እሁዱ ካደረገ በኋላ ከባርሴሎና አሠልጣኝነታቸው በይፋ እንደሚሰናበቱ ቢቢሲ ስፖርት አረጋግጧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here