የዋንጫው መዳረሻ፣ የአሠልጣኞች እና የተጫዋቾች ስንብት

0
233

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሲጠናቀቅ በብዙ ክስተቶች ይታጀባል። አጓጊው የዋንጫ ፉክክር ማንቸስተር ሲቲን ወይም አርሰናልን ያነግሳል። ከምሽቱ የመዝጊያ ጨዋታዎች በኋላም ደሰታ በማንቸስተር ወይም ለንደን ይኾናል። ሌላኛው የመጨረሻዎቹ መርሐ ግብር ድምቀት የአሠልጣኞች እና ተጫዋቾች ከየክለባቸው ስንብት ነው። ሊቨርፑልን ከተረሳበት አንስተው ለፕሪምየር ሊግ እና ሻምፒዮንስ ሊግ ድል ያበቁት የርገን ክሎፕ ዛሬ በአንፊልድ ይሸኛሉ።

በሊቨርፑል ደጋፊዎች ዘንድ አብዝተው የሚወደዱት ሰው ዛሬ በአንፊልድ ከዎልቭስ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይሰናበታሉ። በዚህ ጊዜ የአሠልጣኙ እና የቀሪ ሊቨርፑላዊያን ስሜትም በጉጉት ይጠበቃል። ጣሊያናዊ የብራይተን አሠልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቤ ሌላኛው ከዛሬ ጨዋታ በኋላ ከክለባቸው የሚሰናበቱ አሠልጣኝ ናቸው። አሠልጣኙ በተለይ ባለፈው ዓመት በክለቡ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ በትልልቅ ክለቦች ዐይን ገብተዋል። ዛሬ ብራይተን ከማንቸስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታም የአሠልጣኙ የመጨረሻ ጨዋታ ነው።

በፕሪምየር ሊጉ የመጨረሻ መርሐ ግብር ለክለባቸው የመጨረሻ ጨዋታ የሚያደርጉ ወይም ደጋፊዎቻቸውን የሚሰናቱ ተጫዋቾችም በርካታ ናቸው። የማንቸስተር ዩናይትዱ ራፍይል ቫራን፣ የሊቨርፑሉ ቲያጎ አልካንትራ በይፋ ዛሬ ከክለቦቻቸው ጋር ከሚለያዩት ውስጥ መኾናቸውን ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here