ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት በሚደረጉ 10 ጨዋታዎች ይቋጫል። ከአሥሩ ጨዋታዎች አንዱ ብራይተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ምሽት 12 ሰዓት የሚያደርጉት ይገኝበታል። የብራይተን ዋና አሠልጣኝ ደግሞ ሮቤርቶ ደ ዘርቢ ይባላሉ። እሳቸው የመጨረሻ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ካደረጉ በኋላ ቡድኑን በይፋ እንደሚሠናበቱ ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል።
የቡድኑ ደጋፊዎች ለክብራቸው በነቂስ ስታዲየም በመገኘት ይሸኟቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ዘጋርዲያን እንደዘገበው የ44 ዓመቱ ጣልያናዊ አሠልጣኝ የቀጣይ ማረፊያቸው ማንቸስተር ዩናይትድ አልያም ባየር ሙኒክ ሊሆን ይችላል በሚል ግምቱን አስቀምጧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!