የሀገር ባለውለታው ተጫዋች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

0
298

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በቅፅል ስማቸው “ሻሾ” በሚል በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 60ዎቹ መጀመሪያ በተጫዋችነት አሳልፈዋል።

ኃይለማርያም ለጥቅምት 23፣ ለሸዋ ፖሊስ፣ ለዳኘው እና ለሸዋ ምርጥ ተጫውተዋል። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ተመርጠው ተሰልፈዋል። በዋናው ብሔራዊ ቡድንም ተጫውተዋል ። በተለይ በ1954 ኢትዮጵያ የሦስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍም ኃይለማርያም መኮንን የቡድኑ አባል እንደነበሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ ገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here