ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ ኦሎምፒክ በማራቶን ይሳተፋል።

0
264

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አትሌቲክስ ፌደሬሽን በፓሪስ 2024 ማራቶን አትሌት ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በሁለቱም ጾታ የሚሳተፉ እና ተጠባባቂ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ሲሳይ ለማ እና ዴሬሳ ገለታ ተካትተዋል፡፡

በዚሁ ቡድን አትሌት ታምራት ቶላ እና ኡሰዲን መሐመድ በተጠባባቂነት መካተታቸውን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡ እንዲሁም በሴቶች ማራቶን ትዕግስት አሰፋ፣ አማኔ በሪሶ እና መገርቱ ዓለሙ ሲካተቱ፣ በተጠባባቂነት ደግሞ አትሌት ጎይተቶም ገብረ ሥላሴ እና ቡዜ ድሪባ ተካትተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here