ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በአታላንታ እና ጁቬንቱስ መካከል ተካሂዷል። ጨዋታውን አሮጊቶቹ አንድ ለባዶ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ኾነዋል።
ባለፉት ዓመታት ከዋንጫ ርቆ የነበረው ጁቬ ከሦስት ዓመታት በኋላ ከዋንጫ ጋር ተገናኝቷል። የትናንቱን ጨምሮም ክለቡ ያገኛቸው የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎች ብዛት 15 ደርሷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!