የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለተንታ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።

0
280

ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ተንታ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ለአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት፣ ፕሮጀክቶች፣ ለክልል እና ለከተማ አሥተዳደሮች የትጥቅ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ግንቦት 03/2016 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ ስር ለሚገኘው ለተንታ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አበባ ዮሴፍ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የሂሳብ ባለሙያ ቃልኪዳን ተስፋዬ ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

በስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌትነት መላክ ፣የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሙሳ አዳል፣ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ሥራ አሥኪያጅ ሙሐመድ አለባቸው እና የማዕከሉ አሠልጣኞች ተገኝተው በጋራ የስፖርት ትጥቁን ተረክበዋል፡፡

ለተደረገላቸው ድጋፍም ለፌዴሬሽኑ ምሥጋና ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here