የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ግንቦት 17 የዓለም እግር ኳስ ቀን እንዲኾን አወጀ።

0
196

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የሆነውን ስፖርት እንዲያከብሩ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በየዓመቱ ግንቦት 17 የዓለም እግር ኳስ ቀን ሆኖ እንዲከበር ተወስኗል። በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓዉያን አቆጣጠር ግንቦት 17 ቀን 1924 የተደረገውን ዓለም አቀፉን የእግር ኳስ ውድድር 100ኛ ዓመት የሚታሰብበት እለት መሆኑ ታውቋል። 193 አባላት ያሉት ጠቅላላ ጉባኤው የውሳኔ ሃሳቡን በጋራ ስምምነት የተቀብሎ አጽድቆታል።

ሀሣቡን ለጉባዔው ያስተዋወቁት በሊቢያ የተመድ አምባሳደር ታሄር ኤል-ሶኒ ለጉባኤው እንደተናገሩት እግር ኳስ በዓለም ዙሪያ የሚዘወተር እና ብዙ ተከታይ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሩ እግር ኳስ በሁሉም የእድሜ ክልሎች ያሉ በሙሉ በመንገዶች፣ በመንደሮች እና በትምህርት ቤቶች ለመዝናናት እና ለውድድር ከሚያካሂዷቸው ጨዋታዎች ሁሉ ተወዳጅ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here