ባሕር ዳር: ሚያዝያ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ። በዛሬ መርሐግብርም ፒኤስጅ ከቦሩሲያ ዶርትመንድ ይጫወታል።
ከሳምንት በፊት በነበረው ጨዋታ የጀርመኑ ክለብ በሜዳው አሸናፊ ነበር። ጨዋታውም 1 ለ 0 መጠናቀቁ ይታወሳል። ፒኤስጅ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ያለውን የደካማ ውጤት ታሪክ ለመቀየር የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ ይጥራል። ጨዋታውን በሁለት ግብ ልዩነት ማሸነፍም በቀጥታ ለፍጻሜ ያደርሰዋል።
አሠልጣኙ ልዊስ ሄነሪኬ በመከላከል ይሁን በማጥቃት 90 ደቂቃውን በትኩረት እንጫወታለን ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በአንጻሩ ዶርትመንድ በመጀመሪያው ጨዋታ ባገኘው ድል በመነሳሳት ለፍጻሜ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ የተሻለ እድል በእጁ ይገኛል።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ሰዓት ፓሪስ ላይ ይካሄዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!