ባሕር ዳር: ሚያዝያ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሊጉ 23ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል። ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች 14ቱን ሲያሸንፍ 4 ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪው 4 ጨዋታ አቻ ወጥቷል። በ22 ጨዋታዎች 40 ግቦችን ሲያስቆጥር 21 ግቦችን ደግሞ አስተናግዷል።
በአሠልጣኝ በጸሎት ልዑልሰገድ የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባደረጋቸው ያለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች በ3ቱ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፏል፣ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል። በአምስቱ ጨዋታዎች አምስት ግቦች ተቆጥረውበታል፣ ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሮ አጠቃላይ በሊጉ 46 ነጥቦችን በመሠብሠብ የሊጉ መሪ መሆን ችሏል።
ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በሊጉ እስካሁን ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች ዘጠኝ ጊዜ ሲያሸንፍ በስድስቱ ሽንፈት ገጥሞት ሰባት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በአሠልጣኝ ነጻነት ክብሬ የሚመሩት ቡናማዎቹ በ22 ጨዋታዎች 31 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 23 ግቦችን ደግሞ አስተናግደዋል። ቡናማዎቹ በ34 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በሌላኛው የ23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከሀምበሪቾ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ኢትዮጵያ መድን ባለፉት 5 የሊግ ጨዋታዎች ሳይሸነፍ ሁለት ጊዜ አሸንፎ ሦስት ጊዜ አቻ ተለያይቷል። በሊጎ በሰበሰባቸው 22 ነጥቦች 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሀምበሪቾ ካለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አራት ጊዜ ሲሸነፍ አንድ ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። በስምንት ነጥብ የሊጉን መጨረሻውን ደረጃ ይዟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!