ባሕር ዳር: ሚያዚያ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባየርሙኒክ ከአሁኑ አሠልጣኙ ቶማስ ቱሸል ጋር በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ይለያያል። አዲስ አሠልጣኝ ለመፈለግ ሲወጣ ሲወርድ የነበረው የጀርመኑ ክለብ አሁን ራልፍ ራኝክን ሊሾም ጫፍ መድረሱን ክለቡ አስታውቋል።
በአብዛኛው ድርድሩ የተጠናቀቀ ሲኾን ክለቡን በሚቀላቀሉ እና ከክለቡ በሚወጡ ተጫዋቾች፣ በአጠቃላይም በክለቡ ቀጣይ ፕሮጀክቶች ዙሪያ መነጋገር እና መግባባት በሁለቱ መካከል በቀጣይ ይጠበቃል ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!