ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፈረንሳይ ሊግ አንድ የ2023/24 የውድድር ዘመን ፒ.ኤስ.ጅ በ31 ጨዋታዎች 70 ነጥብ በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡ በሁለተኛነት የሚከተለው ሞናኮን በ12 ነጥብ በመብለጥ ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩት ዋንጫ ማንሳቱን አረጋግጧል፡፡
ፒ.ኤስ.ጂ ለሦስት ተከታታይ የውድድር ዘመን በማሸነፉም ዋንጫውን የግሉ የሚያደረግ ይኾናል፡፡ ቡድኑ ዋንጫ ሲወስድ ይህ ለ12ኛ ጊዜ መኾኑ ነው፡፡ አሠልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በሚቀጥለው ወር በቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚኖራቸውን ጨዋታ በማስታወስ ” ከዚህ በኋላ ፊታችንን ወደ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ እናዞራለን “ማለታቸውን ክለቡ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡
የክለቡ ፕሬዚዳንትም ለተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች፣ ደጋፊዎች እንዲሁም የክለቡ አባላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!” ብለዋል፡፡ በፈረንሳይ ሊግ አንድ 18 ቡድኖች እየተወዳደሩ ሲኾን ብሬስት በ56 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም ሊል በ54 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘው ይገኛሉ፡፡ ሎሪንት በ26 ነጥብ እና ክሌርሞንት በ25 ነጥብ ሦስት ጨዋታዎች እየቀራቸው ወራጅ ቀጣናው ላይ ይገኛሉ ሲል ስካይ ስፖርት አስነብቧል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!