በማድሪድ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው፡፡

0
225

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በስፔን ርእሰ መዲና ማድሪድ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጰውያውያን እና ኬኒያውያን አትሌቶች የበላይነቱን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

የማድሪድን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን እና ኬኒያውያን አትሌቶች መድመቃቸው ነው የተዘገበው፡፡ በወንዶች ማራቶች ኢትዮጵያዊ አትሌት ምትኩ ጣፋ ውድድሩን በ2 ሰአት ከ8 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመጨረስ በአንደኝነት ገብቷል፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ፍቅሬ በቀለ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡

ኬኒያዊ አትሌት ዳግላስ ቼቢ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ተከትሎ በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡ እንደ አፍሪካ ኒውስ ዘገባ ኢትዮጵያዊ አትሌት ምትኩ ጣፋ ከህመም ጋር እየታገለ ነው ውድድሩን ያሸነፈው።

በሴቶች የማራቶን ውድድር የ2023 የናይሮቢ የማራቶን አሸናፊዋ ናኦም ጀቤት በማድሪድ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የማራቶን ድል አስመዝግባለች፡፡ አትሌቷ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ44 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቅቃለች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ቦንቱ በቀለ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ቀበኔ ጫላ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here