ባሕር ዳር: ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፓሪስ ከ2024 የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች መጀመር በፊት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጷጉሜ 3/2016 ዓ.ም የሚቆይ የተለያዩ ትዕይንቶች የተካተቱበት አውደ ርዕይ ተከፍቷል። አውደ ርዕይው ባለፉት 30 ኦሎምፒኮች የነበሩ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ታሪኮችን የሚያስቃኝ ነው ተብሏል።
በርከት ያሉ የጥበብ ሥራዎችን፣ ፎቶግራፎችን እና የፖፕ ባሕልን የሚያሳዩ ቁሳቁሶች ለእይታ ይቀርባሉ ነው የተባለው፡፡ የታሪክ ምሁሩ እና የአውደ ርዕይው አስተባባሪ ስቴፋን ሞርላን አውደ ርዕዩ የነጻነት እና የዲሞክራሲ ትግል ታሪክ ማሳያ እንደኾነም አስረድተዋል።
አውደ ርዕይው “ኦሎምፒዝም የዓለም ታሪክ” በሚል መሪ መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም ድረስ በፓሪስ በሚገኘው የፈረንሳይ የኢሜግሬሽን ታሪክ ሙዚየም ነው ለዕይታ ክፍት የኾነው። የፓሪስ የበጋ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም ሐምሌ 19 እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!