ባሕር ዳር: ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ45 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊው አርኔ ስሎት የሊቨርፑል አሠልጣኝ ለመኾን ከስምምነት ላይ እንደሚደርሱ እርግጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡ አሠልጣኙ የርገን ክሎፕን በመተካት ነው የሊቨርፑል አሠልጣኝ የሚኾኑት፡፡ አሠልጣኝ ስሎት እንዳሉት አሁን ላይ ድርድር ላይ እንዳሉ እና ከስምምነት ላይ እንደሚደርሱም አስረግጠው ተናግረዋል።
አሠልጣኙ ከፌይኖርድ ቡድን ጋር ውላቸው ያልተጠናቀቀ በመኾኑ ሁለቱ ቡድኖች እየተነጋገሩ መኾናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ” ክለቦቹ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ እየጠበኩ ነው፤ እውን እንደሚኾንም ሙሉ እምነት አለኝ” ብለዋል፡፡ ውጤቱን በጉጉት እየጠበቁ መኾናቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ሊቨርፑል በኤክስ ገጹ እንዳለው አሠልጣኝ ስሎት የቡድኑ ተመራጭ አሠልጣኝ ነው ብሏል። ይህም ስምምነቱ አይቀሬነቱን ይጠቁማል ነው የተባለው፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!