ሮቢን ቫን ፔርሲ ወደ አሠልጣኝነት!

0
331

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የአርሰናል እና የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ሮቢን ቫን ፔርሲ የሆላንዱ ሄረንቪን ቡድን ዋና አሠልጣኝ ለመኾን መቃረቡ ተሰምቷል። ሆላንዳዊው ቫን ፔርሲ እግር ኳስን በፕሮፌሽናል ደረጃ መጫወት የጀመረው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2001 ነበር፤ እስከ 2019 ድረስም ክብርና ዝናውን አስጠብቆ በውጤታማነት ተጫውቷል፡፡

በተለያዩ ቡድኖች በ43 ጨዋታዎች ተሰልፎ 204 ግብ ያስቆጠረ ዝነኛ ተጫዋችም ነበር፡፡ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድንም በ102 ጨዋታዎች ተሰልፎ 50 ግቦችን ማስቆጠሩን ዴይሊ ሜይል ስፖርት በዘገባው አስታወሷል፡፡ ቫን ፔርሲ ፊቱን ወደ አሠልጣኝነት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2020 አዙሮ በረዳት እና በተባባሪ አሠልጣኝነት የፌይኖርድን ቡድን አሠልጥኗል፡፡

አሁን ደግሞ የኤስሲ ሄረንቪን ቡድን ለማሠልጠን ተስማምቷል ነው የተባለው፡፡ በቅርቡም ሥራውን ይጀምራል መባሉን የዘገበው ዴይሊ ሜይል ስፖርት ነው፡፡ ቡድኑ በደች ኤር ዲቪን 10ኛ ደረጃ ላይ ስለሚገኝ ቫን ፔርሲ በሚቀጥሉት ጨዋታዎች ቡድኑን ወደ አሸናፊነት የመመለስ ከባድ ኃላፊነት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here