ባሕር ዳር: ሚያዚያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር በአራተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎችን በተመለከተ ለብዙኅን መገናኛ አባላት ማብራሪያ ሰጥቷል።
በዚህም ያለፉት ሁለት ዓመታት የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው እና ለአሠልጣኞቻቸው ለደሞዝ እንዲሁም ለማበረታታት ያወጡት አጠቃላይ ወጪ ታሳቢ ተደርጎ በ2017 አንድ ክለብ ለደሞዝ 52 ሚሊዮን ብር ለማበረታቻ ደግሞ 5 ሚሊየን ብር በድምሩ ከ57 ሚሊየን ብር ዓመታዊ ወጪ በላይ እንዳያወጡ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!