ዣቪ ሄርናንዴዝ በባርሴሎና አሠልጣኝነት ለመቀጠል ተስማማ።

0
269

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ስፔናዊ አሠልጣኝ ዣቪ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ክለቡን እንደሚለቅ ማሳወቁ ይታወሳል። ባርሴሎናም ዣቪን ለመተካት የተሻለ አሠልጣኝ ከማፈላለግ ጎን ለጎን የስፔናዊን ሀሳብ ለማስቀየር ሢሠራ ቆይቷል።

ሞንዶ ዲፖርቲቮ አንደ ዘገበው ዣቪ የክለቡን ቆይልን ጥያቄ ተቀብሏል። የድሮው የክለቡ ተጫዋች በ2023 የውድድር ዘመን ክለቡ የላሊጋ ዋንጫ እንዲያነሳ ማድረጉ ይታወሳል።

ነገር ግን በዘንድሮው የውድድር ዘመን ክለቡ ደካማ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በዚህ ትችት የደረሰበት ዣቪ ባለፈው ጥር ክለቡ ለውጥ እንደሚያስፈልገው በመናገር በውድድሩ የመጨረሻ ዓመት ከክለቡ እንደሚለያይ ይፋ አድርጎ ነበር።

በመጨረሻ ግን ከክለቡ ኀላፊዎች ጋር በመነጋገር አሠልጣኙ በክለቡ ለመቆየት ወስኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here