ባሕር ዳር: ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ ሳኦት የተባለውን አዲስ የጨዋታ ውጪ (off site) ቴክኖሎጂ ለመሞከር በሙሉ ድምጽ ተሰማምቷል።
ይህ ቴክኖሎጂ ከጨዋታ ውጪ እንቅስቃሴ ሲታይ በፍጥነት መስመር በማስመር ያሳውቃል። በየውሳኔው እስከ ሰላሳ ሰከንድ ድረስ ብክነት የሚቀንስ ይኾናልም ተብሏል።
በአዲሱ ቴክኖሎጂ የጨዋታ ረዳት ዳኞች ከጨዋታ ውጪ እንቅስቃሴ በሚኖርበት ጊዜ ሳኦት በመባል ከሚጠራው ቴክኖሎጂ የድምጽ መልዕክት እንደሚደርሳቸው እና አርማቸውን በማውለብለብ ውሳኔ እንደሚሰጡ የስፖርት ስታርስ መረጃ ያሳያል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!