ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ አንድ ቢሊዮን ብር ተጠይቆ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ መፈቀዱን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገልጿል።
ከተፈቀደው ገንዘብ 400 ሚሊዮን ብር በሩብ ዓመቱ ሥራ ላይ መዋሉን በቢሮው የእቅድ ዳይሬክተር አገሬ ሰንደቁ ገልጸዋል።
ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅደ ትውውቅ እና የአንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደም ይገኛል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!