በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄዱ የተለያዩ የባሕል ስፖርቶች የአማራ ክልል ስፖርተኞች ድል ቀንቷቸዋል።

0
395

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 21ኛው የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች ውድድር እና 17ኛው የባሕል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ በተደረጉ የሴቶች የትግል ስፖርት ውድድር ከ58 ኪሎ ግራም እስከ 62 ኪሎ ግራም አማራ ክልል ኦሮሚያ ክልልን፤ ከ53 ኪሎ ግራም እስከ 57 ኪሎ ግራም አማራ ክልል የሲዳማ ክልልን እንዲሁም ከ68 ኪሎ ግራም እስከ 72 ኪሎ ግራም አማራ ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን አሸንፏል።

ይህ የትግል ስፖርት ውድድር በወንዶችም ቀጥሎ የዋለ ሲኾን ከ53 ኪሎ ግራም እስከ 57 ኪሎ ግራም አማራ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። ውድድሩ በባለ18 ጉድጓድ የሴቶች ገበጣ ጨዋታም አማራ ክልል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን 2 ለ 0 ረትቷል።
የአማራ ከልል እና የኦሮሚያ ክልል በ12 ጉድጓድ የወንዶች ገበጣ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

አማራ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል ባደረጉት የገና ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ ተለያይተዋል። በበሻህ የሴቶች ውድድርም አማራ ክልል ሲዳማ ክልልን እንዲሁም በበሻህ የወንዶች ጨዋታ አማራ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በተመሳሳይ 2ለ0 አሸንፏል።

በቡብ የሴቶች ውድድር አማራ ክልል እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም በወንድ አማራ ክልል ከሲዳማ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። የፈረስ እና የኩርቦ የፍጻሜ ውድድሮች ነገ ይካሄዳሉ ሲል የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here