የቼዝ ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን የተደረገ ጨዋታ።

0
208

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ናይጄሪያዊው የቼዝ ተወዳዳሪ እና የሕጻናት ትምህርት ጉዳይ ተሟጋች ቱንዴ ኦናኮያ ረጅሙ የቼዝ ማራቶን ክበረ ወሰን ባለቤት መሆን የሚያስችለውን ጨዋታ አከናውኗል። ኦናኮያ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ከዚህ በፊት የተያዘውን ሪካርድ ለመስበር በማሰብ በኒውዮርክ ከተማ ጨዋታ አድርጓል። ጨዋታው በታይምስ አደባባይ ላይ ለ60 ሰዓታት ያለማቋረጥ ነበር የተካሄደው።

የ29 ዓመቱ የቾዝ ተወዳዳሪ ኦናኮያ በመጀመሪያ ለ58 ሰዓታት ለመጫወት አቅዶ ነበር። ነገር ግን ከዚህ በላይ መጫወት ችሏል። የዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ መመሪያን መሰረት ባደረገ መልኩ ኦናኮያ ከአሜሪካው የቼዝ ሻምፒዮን ሾን ማርቲኔዝ ጋር ነበር ጨዋታውን ያደረገው።

በመመሪያው መሰረት ሪከርዱን ለመስበር ሁለቱ ተጨዋቾች ያለማቋረጥ ከተመዘገበው ሰዓት አልፈው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ኦናኮያ ባደረጓቸው ጨዋታዎች በሙሉ አሸናፊ በመሆን ነው ለስድሳ ሰዓታት የዘለቀው፡፡ በአንድ ሰዓት የጨዋታ ቆይታ ውስጥ የአምስት ደቂቃ እረፍት ብቻ ነበር የተሰጣቸው።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የእረፍት ጊዚያት ተደማምረው እንደ አንድ የፋታ መውሰጃ ሆኖ ይሰጣቸው ነበር ። በዚህ አጋጣሚ ኦናኮያ እሱን ለማበረታታት በስፍራው ከተገኙ ናይጄሪያውያን ጋር ይገናኝ ነበር ። የኒውዮርክ ነዋሪዎችም አበረታተውታል። ኦናኮያ ያስመዘገበው ሰዓት በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገበ ድርጅት ከተረጋገጠለት ረጅሙ የቼዝ ማራቶን ሪከርድ ባለቤት ይሆናል።

አሁን ላይ በቼዝ ማራቶን የተያዘው ክብረ ወሰን 56 ሰአት ከ9 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ ነው። ኦናኮያ ክብረወሰን ከማስመዝገብ ጎን ለጎን ለሕጻናት ትምህርት ድጋፍ የሚውል 1 ሚሊዮን ዶላር የማሰባሰብም ግብ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here