ባሕር ዳር: ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ተሳትፎ ያደረጉት ኢትዮጵያውያን ቦክሰኞች ስድስት ሜዳሊያዎችን በመሠብሠብ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
በውድድሩ ሦስት የብር እና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎች ስለመገኘታቸው ነው የተመላከተው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው የማንዴላ መታስቢያ ውድድር ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ቦክስ ብሔራዊ ቡድን በ54 ኪሎ ግራም በሱራፌል አላዩ፣ በ60 ኪሎ ግራም በሚሊዩን ጨፎ እና በ66 ኪሎ ግራም በቤተል ወልዱ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል፡፡
በ50 ኪሎ ግራም በቤተልሄም ገዛህኝ፣ በ54 ኪሎ ግራም በሮማን አስፋ እና በ75 ኪሎ ግራም በተመስገን ምትኩ የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቃለች፡፡
የልዑካን ቡድኑ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ ከባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ ልዑካን ቡድኑ ወደ ሀገሩ ሲገባ በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታልም ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!