ባሕር ዳር: ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ናጌልስማን የጀርመን ብሔራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድንን ማሠልጠን የጀመረው እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ከ2023 ጀምሮ ሲኾን በሐምሌ 2024 ደግሞ የሥራ ውሉ ይጠናቀቃል ሲል አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ይህን ተከትሎም ሰውዬው ወደ ባየርሙኒክ ሊያመራ ይችላል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ይሁን እንጅ የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚዳንት በርንድ ኑኢንዶርፍ እንዳሉት የናጌልስማን ውል እስከ 2026 የዓለም ዋንጫ ድረስ ተራዝሟል ብለዋል።
አሠልጣኝ ናጌልስማን በውል ሰነዱ ላይ ከፈረመ በኋላ “የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን ማሠልጠን ትልቅ ክብር ነው፤ ስለዚህ ውሳኔውን ከልቤ ወድጄዋለሁ” ሲል ተናግሯል። የ36 ዓመቱ ናጌልስማን በ2023 ሃንሲ ፍሊክን ተክተው መሾማቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!