በማንዴላ መታሰቢያ የቦክስ ዋንጫ ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ነው፡፡

0
270

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመጀመሪያው የማንዴላ መታሰቢያ የአፍሪካ የቦክስ ዋንጫ በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ነው። ውድድሩን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን እና የደቡብ አፍሪካ የቦክስ ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ሲኾን በአህጉሩ ልዩ የቦክስ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ይፈሩበታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የዓለም የቦክስ ማኅበር ፕሬዚዳንት ዑመር ክሬምሌቭ እንዳሉት የማንዴላ መታሰቢያ የቦክስ ዋንጫን በታላቁ የደቡብ አፍሪካ መሪ ኔልሰን ማንዴላ ሀገር በማድረጋችን ደስ ብሎናል። የማንዴላ የሰላም እና የአብሮነት መልዕክት አሁንም በስፖርት ተሳትፎ እየተስተጋባ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
በዚህ ውድድር ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 12 ሴት እና 13 ወንድ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ የክብደት ምድቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ኢትዮጵያዊቷ ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ በ54 ኪሎ ግራም የናሚቢያ ተጋጣሚዋን በመጀመሪያው ዙር በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ የማንዴላ መታሰቢያ የቦክስ ዋንጫ ስያሜው ፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ያደረጉትን የነጻነት ተጋድሎ እና የሰላም ስምምነት ለማስታወስ ነው፡፡

ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓት በነበረበት ወቅት የቦክስ ስፖርትን ሠልጥነው ዘርፉን ለፀረ አፓርታይድ ትግል ይጠቀሙበት እንደ ነበርም ልብ ይሏል፡፡ ኢንሳይድ ዘ ጌምስ በድረ ገጹ እንዳስነበበው የማንዴላ መታሰቢያ የቦክስ ዋንጫ ሽልማት 500 ሺህ ዶላር ነው። ውድድሩ ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም የተጀመረ ሲኾን እስከ ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም የሚቀጥል መኾኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here