አዲስ አበባ: ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አቶ ቢልልኝ መቆያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተካሄደ ሥብሠባ የአፍሪካ የቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ኾነው ተመርጠዋል። በስፖርቱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ ልምድ ያካበቱት ቢልልኝ መቆያ በአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን የቦርድ አባላት በሙሉ ድምጽ ነው የተመረጡት።
በውጤት የተደገፈ እና ባለ ብዙ ችሎታ ያለው የስፖርት አሥተዳዳሪ ኾነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ቢልልኝ መቆያ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አማካሪ በመኾንም አገልግለዋል። የቅርጫት ኳስ አሠልጣኝም በመኾን በማስተማር እና ብቁ የኾነ የስፖርት ባለሙያ በመኾንም ሠርተዋል፡፡
የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን እና ሰፊው የአፍሪካ የዘርፉ ስፖርት ማኅበረሰብ አቶ ቢልልኝ መቆያ ውጤት እንዲያመጡም ተመኝተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!