ባሕር ዳር: ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገሪቱ እግርኳስ የበላይ አካል የኾነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዳኞች ኮሚቴነት ሢሠሩ የቆዩትን አባላት በማሰናበት ኮሚቴውን በአዲስ መልክ አዋቅሯል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአልቢትር ኮሚቴነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዮ አባላትን በአዲስ መልክ በተሻሻለው መተዳደርያ ደንብ መሰረት መነሳታቸው ተገልጿል።
በዚህም መሠረት ሠብሣቢው ሸረፋ ዴሌቾን ጨምሮ አራት የኮሚቴው አባላትን አሰናብቷል፡፡ በምትካቸውም በቀጣይ ዓመታት ኮሚቴውን በበላይነት እንዲመሩ በቅርቡ እራሳቸውን ከዳኝነት ያገለሉትን የቀድሞ ኢንተርናሽናል አልቢትሮች ለሚ ንጉሴ፣ ክንዴ ሙሴ፣ ሊዲያ ታፈሰ፣ ሸዋንግዛው ተባባል እና ክንፈ ይልማ ኮሚቴውን እንዲመሩ መድቧል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ እንደዘገበው የኮሚቴው ሠብሣቢ በመኾን ሸዋንግዛው ተባባል መመረጣቸው ታውቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!