ፒኤስጅ ከባርሴሎና የሚገናኙበት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል።

0
227

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት ምሽት የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጠበቁት ልክ ያዝናኑት ሁለቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች አቻ ተጠናቀዋል።የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ቡድኖችን ለመለየት እየተደረጉ ያሉ የሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ። ፒኤስጅ ከባርሴሎና፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትሙንድ ይጫወታሉ።

የፈረንሳዩ ፒኤስጅ በሜዳው የስፔኑ ባርሴሎናን የሚገጥምበት ጨዋታ ትኩረት ስቧል። በቀድሞው የባርሴሎና ተጫዋች እና አሠልጣኝ ሊዊስ ሄነሪኬ የሚመራው ፓሪሰንዠርሜ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከፍተኛ ፋላጎት አለው። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ኮከቦችን ሰብስቦ አልተሳካለትም።
መሲ እና ነይማርን የመሳሰሉ ኮከቦችን የሸኘው ይህ ቡድን በውድድሩ ለመድመቅ በፈረንሳያዊ ኪሊያን ምባፔ ላይ ትልቅ ተስፋ ጥሎ ባርሴሎናን በማሸነፍ ለቀጣይ በረዝሙ አልሟል።

ባርሴሎና በላሊጋው ዘንድሮ ዋንጫውን የሚያገኝ አይመስልም። በዓመቱ መጨረሻ ከአሠልጣኛቸው ዣቪ ጋር የሚለያዩት ባርሴሎናዎች ዓመቱን በዋንጫ ለማጠናቀቅ ብርቱ ጥረት የሚያደርጉትም በሻምፒዮንስ ሊጉ ነው።

እናም አሠልጣኙ ዣቪ “ለዚህ ጨዋታ በጥሩ መነሳሳት ላይ እንገኛለን” ማለቱን ቢቢሲ አስነብቧል። የፒኤስጅው አሠልጣኝ ሊዊስ ሄነሪኬ ደግሞ “ባርሴሎና እና ዣቪን በደንብ አውቃቸዋለሁ ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እንዳርጋለን” የሚል ሀሳብ ሰጥቷል።

በሌላ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትሙንድ ይገናኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች በየሀገራቸው ሊጎች የተቀዛቀዘ የውድድር ዓመትን እያሳለፉ ነው። ነገር ግን በሻምፒዮንስ ሊግ በምድብም ኾነ በጥሎ ማለፋ ጨዋታዎች የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየት ችለዋል። በተጨማሪም ቡድኖቹ ተመጣጣኝ የሚባል አቋም ላይ የሚገኙ በመኾናቸው የተሻለ የመሸናነፍ ትግል እንደሚታይበት ጎል የመረጃ ምንጭ ዘግቧል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here