ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬ መርሐ ግብር የተሻለ ፉክክር እንደሚታይባቸው የሚጠበቁ ጨዋታዎች ይስተናግዱበታል።
ቀን 10 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ። ኢትዮጵያ ቡና በ30 ነጥብ በሰንጠረዡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሀዋሳዎች በበኩላቸው በ26 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ምሽት አንድ ሰዓት በሚጀምር ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን ይገጥማል። አጼዎቹ በሊጉ መሪነት ከሚገኙ ቡድኖች ለመቅረብ አስበው ጨዋታውን ያደርጋሉ። ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ 10ኛ ላይ ይገኛል። የሠበሠበው ነጥብ ደግሞ 26 ነው። በዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉም የደረጃ መሻሻል ያሳያሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!