የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ኾነ።

0
336

ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የመጋቢት ወርን የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ከአፍሪካ ሞሮኮ በዓለም 13ኛ በአፍሪካ ደግሞ በመሪነት ተቀምጣለች። ሴኔጋል ከዓለም 17ኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ ኾናለች።

በቅርቡ በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚዋ ናይጄሪያ ከዓለም 30ኛ ከአፍሪካ የሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በዓለም 38ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ግብጽ ከአፍሪካ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮና ኮትዲቯር ከዓለም 38ኛ ስትኾን ከፍሪካ አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን የዘገበው ካፍ ኦንላይን ነው። የዓለምን እግር ኳስ በመጋቢት ወር 2024 አርጀንቲና በግንባር ቀደምትነት ትመረዋለች። ፈረንሳይ ሁለተኛ ስትኾን ፣ቤልጀየም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች በማለት የዘገበው ካፍ ኦንላይን ነው።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here