ባሕር ዳር: መጋቢት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኙት አርሰናል እና ማንቸስተር ሲቲ ተፎካካሪነታቸውን የሚያጠነክሩበትን ውጤት አስመዝግበዋል።
በሜዳው ሉተንን የገጠመው የአርቴታው አርሰናል 2 ለ 0 ረቷል። ነጥቡን 68 በማድረስም የሊጉን መሪነት አንድ ጨዋታ አንሶ ከተጫዎተው ሊቨርፑል ተረክቧል።
በተመሳሳይ ማንቸስተር ሲቲ ይፈተንበታል የተባለውን ጨዋታ በቀላሉ አሸንፏል። ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ የሚጫወተው አስቶን ቪላ ሲቲን እንደሚፈትን ግምት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል።
ምሽቱን በተካሄደ ሌላ ጨዋታ ብሬንት ፎርድ ከብራይተን አቻ ተለያይተዋል።
ፕሪምየር ሊጉ ዛሬም ሲቀጥል ማንቸስተር ዩናይትድ ከቸልሲ እንደሚጫወቱ ቢቢሲ አስነብቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!