ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በዛሬ መርሐግብር አርሰናል ከሉተን፣ ማንቸስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከብራይተን ይጫወታሉ።
አርሰናል በሜዳው ሉተንን የሚገጥምበት ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝ ነው። በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው አርሰናል ተፎካካሪነቱን ለማጠንከር፣ ወራጅ ውስጥ የሚገኘው ሉተን ደግሞ በሊጉ ለመቆየት ውጤት አብዝተው ይፈልጋሉ።
በተመሳሳይ የማንቸስተር ሲቲ እና አስቶን ቪላ ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ሲቲዎች ከመሪዎቹ ይበልጥ ለመቅረብ፣ ቪላዎች ደግሞ የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማግኘት በዛሬው ጨዋታ ለውጤት ይፋለማሉ።
በፕሪምየር ሊጉ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ቶትንሃም እና ዌስተሃም ፣ኒውካስትል ከኤቨርተን እንዲሁም በርንለይ ከወልቭስ በተመሳሳይ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ኖቲንግሃም ፎረስት ፍልሃምን፣ በርንማውዝ ፓላስን አሸንፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!