ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግሥት የተበረከተላቸውን የወርቅ ጨረር ያለውን ኒሻን ሽልማታቸውን ተረክበዋል። ይህ እውቅና እና ሽልማትእንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሀገር ዜጎች በጃፓን መንግሥት የሚሰጥ አንጋፋ እና ክብር ያለዉ ነው::
ከኢትዮጵያ የወርቅ ጨረር ያለው ኒሻን ሽልማት ከጃፓን መንግሥት ሲሰጥ ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ ናቸው። በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርት ዲፕሎማሲ እና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ ፣ በሌሎች ሀገራት እና አካባቢዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ፣ ለአትሌቲክስ እድገት፣ ለሀገር ሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅ እና በመስጠት በዓለም አቀፍ መስኮች የላቀ ስኬት ምክንያት ሽልማቱን አግኝተዋል።
ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ሽልማታቸውን በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እጅ ተረክበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!