በዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የወከለው ልዑክ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል ተደረገለት።

0
270

ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰርቪያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛው ዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ልዑኩ ዛሬ ማለዳ ሀገሩ የገባ ሲሆን የኢፌዴሪ ባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል ።

በውድድር ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በ28 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን በሁለት ወርቅ ፣በስድስት ብር እና በሁለት ነሃስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያ ከዓለም የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ውድድሩርን ጨርሳለች ፡፡

ለአትሌቲክስ ልዑኩ ከተደረገለት አቀባበል በኋላ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እውቅና እና ሽልማት ይበረከትለታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here