በኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ዛሬ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

0
251

ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛ ሳምንቱ ላይ በደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ዘጠኝ ሰዓት ላይ መቻል እና አዳማ ከተማ ይገናኛሉ። በሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት የሚችለው ቡድን ፕሪሜር ሊጉን ይመራል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ባሕር ዳር ከነማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። በስድስተኛ ሳምንት መርኃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስን የረቱት የጣና ሞገዶቹ በጥሩ መነሳሳት ላይ ኾነው ሀዋሳን እንደሚገጥሙ ተጠብቋል።

የሸገር ደርቢ በቅድሥ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ነገ 9 ሰዓት የሚከናወን ይኾናል።

በአስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here